አገልጋዮች

ሐዋርያ ቦአኔርጌስ እሸቱ(ቦርን) በአፖስትል ቦርን ሚኒስትሪስ እና በዙፋኑ ሕይወት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን በሐዋርያዊ ፀጋ በመሪነት የሚያገለግል ሲሆን ላለፉት 19 ዓመታት በተጠራበት መልእክተኛነት በእግዚአብሔር ፀጋና ሃይል ፥

በኢትዮጲያ፦ በሁሉም ክልል በመዘዋወር

በአፍሪካ፤በሰሜን ሱዳን(ካርቱም)

በአውሮፖ፦ ዴንማርክ፣ ሲውዲን፣ፈረንሳይ፣ሲውዘርላንድና ጀርመን ።

ወንጌልን በመስበክ፣ቤተክርስቲያን በመትከልና ሌሎችን በመተካት አገልግሏል።

በአሁኑ ሰዓት ደግሞ መቀመጫውን በሰሜን አሜሪካ፥ዳላስ፡ቴክሳስ በማድረግ ትውልዱ ለሚመጣው ሙሽራ እንዲዘጋጅና የመጨረሻውን የፀጋ ወንጌል እንዲገለጥ በመገናኛ ብዙሃን በፌስቡክ፣ በዩቲውብ፣በቲክ ቶክ በቴሌግራም ፣ በቴሌ ኮንፈረንስ ፣በኤልሻዳይ ቴሌቪዥን እና በኢቫንጄሊካል ቲቪ ፥፡ እንዲሁም የዙፋኑ ሕይወት አለም ዓቀፍ ቤክን ዳላስ፡ቴክሳስ በመትከል የመልእክቱን ተደራሽነት በማስፋፋት ብዙዎችን በእውነት ቃል በማስተማርና በማስታጠቅ ፣አገልጋዮችን በማሰልጠን ፣ በጌታ ጸጋ በተአምራት፣ በፈውስ፣በነጻ ማውጣት፣ በምክር ቃል በማገልገል ለብዙ ሺህ ህዝብ ወንጌል መድረስና ጌታን መቀበል ምክንያት እየሆነ ይገኛል።

ሐዋርያ ቦአኔርጌስ እሸቱ(ቦርን)

ብሩካን ናችሁ

Scroll to Top