እምነታችን

አዕማድ እምነቶች 

እግዚአብሔር አብ

Apostle Born Ministries እግዚአብሔር አብ የሁሉ ፈጣሪ፣ እውቀቱና ችሎታው የማይወሰን፣ በፈቃዱ ሁሉን የሚመራ፣በሰማይና በምድር የወደደውን የሚያደርግ፤ ከልካይም ፈቃጅም የሌለው ልዑል አምላክ እንደሆነ፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን እና በፍጹም ቅድስና የሚኖር በፍቅር የተሞላ፤ ታማኝና መሃሪ አምላክ እንዲሁም ዘላለማዊ መሆኑንና ዓለምን ለማዳን አንድ ልጁን ወደ ዓለም የላከ አዳኝ እንደሆነ እናምናለን እናስተምራለን፡፡

 

(መዝ 24፡1፤ ኢሳ 45፡5-10፤ ዳን 4፡35፣ ማቴ 10፡29፤ ዮሐ 1፡18፣ 3፡16፤ ሐዋ 3፡25-26፣ 17፡26፤ 1ጢሞ 6፡15-16፤ ኤፌ 1፡1፤ 1ዮሐ 1፡18)

ABMONE Ministry Services

እግዚአብሔር ወልድ (ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ)

Apostle Born Ministries ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አብ አንድያ ልጅ፤ ከአብ ጋር ለዘላለም የኖረ አምላክ፤ ዓለም በእርሱ በኩል የተፈጠረ፤ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በሥጋ ከድንግል ማርያም የተወለደ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ሆኖ (መለኮቱና ትስብእቱ ሳይዋዋጡና ሳይከፋፈሉ) ሁለቱን ባህርያት በአንድ አካል የያዘ፤ በምድር ላይ ያለ ኃጢአት የኖረ፤ ወንጌል እየሰበከ፤ ድውያንን እየፈወሰ፤ ሙታንን እያስነሳ፤ በጎ ሥራ እያደረገ የተመላለሰ፤ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል መካከለኛ የሆነ ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ የሞተ በሦስተኛው ቀን በኃይልና በክብር ከሙታን የተነሳ፤ወደ ሰማይ በክብር ያረገ፤ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ስለ እኛ የሚማልድ፤በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ በመላእክት ታጅቦ በክብርና በግርማ ወደ ምድር ተመልሶ የሚመጣ እንደሆነ እናምናለን እናስተምራለን፡፡

(ማቴ 1፡20-21፤ ሉቃ 2፡5-7፣ 3፡16፤ ዮሐ1፡14-18፣ 6፡68-69፣ 8፡58፤ 1ቆሮ 1፡30፤ ቆላ 1፡1-4፣ 3፡1፤1ጢሞ 2፡5፤3፡16፤ 1ዮሐ 1፡1-3፤ዕብ 13፡ 8)

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ

Apostle Born Ministries እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር የተካከለ አምላክ መሆኑን፤በሁሉ ቦታ የሚገኝ ፈጣሪ መሆኑን፤ አማኞችን ወደ እውነት ሁሉ የሚመራ የሚያጽናና እንደ ፈቃዱም የጸጋ ስጦታዎችን ለምዕመናን የሚሰጥ፤በእነዚህ ስጦታዎቹ አማካኝነት በሁሉ ዘመን እየሠራ ቤተክርስቲያንን የሚያንጽ ስለ ክርስቶስ የሚመሰክር ዓለምን ስለኃጢአት፤ ስለ ጽድቅ ስለ ፍርድ የሚወቅስ መሆኑን ያምናል፡፡ አማኞች በኃጢአት ሲመላለሱ መንፈስ ቅዱስ ማዘኑን ስለዚህ አማኞች በሕይወት ንጽሕና እንዲኖሩ መንፈስ ቅዱስ ጸጋ እንደሚሰጣቸውና ለአገልግሎታቸውም ኃይልን እየሰጠ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ሙላት እንደሚያሳድጋቸውም እናምናለን እናስተምራለን፡፡

 

(ኢዮ 33፡4፤ መዝ.139፡7-10፤ ዮሐ 14፡15-16፡26፤ ዮሐ 15፡26)

ብሩካን ናችሁ

Scroll to Top