ስለ እኛ
አፖስትል ቦርን ሚኒስትሪስ እንዴት ተጀመረ?
አፖስትል ቦርን ሚኒስትሪስ እንደ መለኮት የተስፋ ቃል በመጨረሻው ዘመን የምትነጠቀውን ለሚመጣው ሙሽራ (ለክርስቶስ) ዝግጅት ሙሽሪትን(የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን) ማንቃት እና የመጨረሻውን የጸጋና የመንግስቱን ወንጌል ክብር የሚገልጥ ትውልድ ለማየት በመንፈስ ቅዱስና በመልዕክት ቃል በዩሃንስ ወንጌል14፥1-3 ራዕ4፥1 ተመስርቶ መልዕክቱን(ጥሪውን) በተቀበለ በሐዋርያ ቦአኔርጌስ እሸቱ (ቦርን) እና በወቅቱ ጥቂት በነበሩ ወገኖች በሲዊድን ተጀምሮ በ2017 በሰሜን አሜሪካ በፌዴራል መንግስት IRC ተመዝግቦ 501c3 በማግኘት፤እንዲሁም በኢትዮጵያ በ2016 በካውንስሉ ተመዝግቦ ፈቃድ በማግኘት እየተንቀሳቀሰ ያለ አገልግሎት ነው።
ተልዕኮ
1- ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ ስር እንዲሰዱና እንዲመላለሱ ማድረግ።
2-ትምህርቶችን በአካልና በመገናኛ ብዙሃን መስጠት።
3-ሰዎች ጸጋቸውን እንዲያውቁና በዚያም ጸጋ እንዲገለጡ ማገዝና እውቅና መስጠት።
4-በሚቀጥል የእግዚሃብሄር መንግስት ላይ ትኩረት በማድረግ ወንጌልን መስራት።
5-በጉን ክርስቶስን ማፍጠንና ማስቸኮል።
6-እውነተኛ የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀመዝሙር ማፍራት።
7-በእውነት እና በመንፈስ ማምለክ።
8-ለሚድኑ የሂዎት ሽታ ለሚሞቱት የሞት ሽታ መሆን።
9-የእግዚአብሔርን መልክ መድረስ(ሰዎችን ማገዝ)
ዓላማ
1-ትውልዱ ከሚነጠቁት ከጥቂቶቹ ወገን ሆኖ እንዲገኝ ማንቃት።
2-ትውልዱ ከምድር ተስፈኝነት ተላቆ የሚመጣውን አለም ተስፋ እንዲያደርግ በእግዚአብሄር ቃል አይኑን መክፈት ነው።
3-የሰዎችን ሃሳብና መንገድ በእግዚአብሄር አሳብና መንገድ መዋጀት።
4-የልጁን መልክ ብቻ ይዘው እንዲገኙ ሌሎችን መልኮች በማፍረስ ክርስቶስን መሳል ነው።
እሴቶች
1 የመለኮትን ፈቃድ ማስቀደም
2 መልእክተኛነታችን
3 ሕብረት እና አንድነት
4 የእግዚአብሔር ቃል
5 የጾምና የጸሎት ሕይወት
6 ወንጌልን መስበክ
7 አስራትና በኩራት፤መባና የፍቅር ስጦታ መስጠት
8 በታማኝነት ማገልገል
9 ምስጋናና አምልኮ
10 ድሆችን ማገዝ
11 ቅንነትና በጎ ህሊና
12 ሚስጢር ጠባቂነት
13 ትጋትና ልባምነት
14 ቅድስና እና መታዘዝ
15 ግልጽነትና ቀጥተኝነት
16 የጌታ ራት